ማስታወቂያ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ከዚህ በታች በተገለጹት ክፍት የስራ መደቦች ላይ ሥራ ፈላጊዎችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ከዚህ በታች በተገለጹት ክፍት የስራ መደቦች ላይ ሥራ ፈላጊዎችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል። ማሳሰቢያ፡- 1. ከዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ በላይ የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃ ያላቸው አመልካቾች ማመልከት ይችላሉ፡፡ 2. የምዝገባ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ይሆናል፡፡ 3. የሕግ ትምህርት ዝግጅት ያላችሁ ተወዳዳሪዎች ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሁም በሌሎች የትምህርት መስኮች ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የዲግሪ የትምህርት ማስረጃ የሚያቀርቡ ተወዳዳሪዎች የመውጫ ፈተና ያለፉበትን መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 4. የቴክኒክና ሙያ በደረጃ የሚወዳደሩ አመልካቾች የCOC ምዘና ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 5. ከግል ተቋማት የሚቀርቡ የስራ ልምድ ማስረጃዎች የስራ ግብር የተከፈለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል። 6. አመልካቾች ለሚያቀርቡት የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ ህጋዊነት ኃላፊነት ይወስዳሉ። 7. ለፈተና ለሚመለመሉ አመልካቾች ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ በማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል። 8. የምዝገባ አድራሻ: https://forms.gle/wUhHJuMohcbtnzAw9 የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን