#ማስታወቂያ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርትና እና ስልጠና ባለስልጣን የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ከሚያግዙ የተለያዪ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ዘዴዎች መካከል አንዱ የሆነውን የፈቃድ አሰጣጥ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ መመሪያ እና ስታንዳርድ አጸድቆ ስራ ላይ አውሏል፡፡ በዚህም መሠረት በከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/2016 አንቀጽ 4(26) መሠረት በሁሉም የመንግስት ዪኒቨርሲቲዎች እና በሁሉም በክልል መንግስታት ለሚተዳደሩ የከፍተኛ ትምህርት ቋማት ላይ ዳግም ምዝገባ ለማድረግ ዝግጅታችንን አጠናቀን በአተገባበሩ ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ለግማሽ ቀን የሚቆይ የውይይት መድረክ በትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ አዘጋጅተናል፡፡ ስለሆነም በመድረኩ ላይ የሚሳተፍ የተቋሙን አንድ ከፍተኛ አመራር ትልኩ ዘንድ እየጠየቅን የውሎ አበልም ሆነ የትራንስፖርት ወጪ የማንሸፍን መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ