ለባለሥልጣኑ አራት ፕሮግራሞች የተመደበ በጀት አጠቃቀም እና አስተዳደር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያአዳራሽ ለባለሥልጣኑ አራት ፕሮግራሞች ለሥራ አመራር፤ ለእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን፤ለቁጥጥርና ኢንስፔክሽን እና ለፈቃድና ጥራት ኦዴት ፕሮግራሞች የተመደበ በጀት አጠቃቀም እና አስተዳደር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በየደረጃው ለሚገኙ የባለሥልጣኑ አመራሮች ተሰጥቷል። የባለስልጣኑ ስራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ታደሰ ስልጠናውን በንግግር ሲከፍቱ እንዳሉት ለሥራ አመራር፤ ለእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን፤ለቁጥጥርና ኢንስፔክሽን እና ለፈቃድና ጥራት ኦዴት ፕሮግራሞች የተመደቡትን በጀቶች በበቂ ግንዛቤ ላይ በመመሥረት በባለቤትነት፣በአግባቡ መጠቀም እና ማስተዳደር ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። የሀብት አጠቃቀምን በመወሰን ቁልፍ የልማት ፖሊሲ መሳሪያ ሆኖ ማገልገል ፤የአንድ ሀገር ኢኮኖሚን ማረጋጋት፤ የመንግሥት ሀብትን ማደላደል ፤ የመቆጣጠሪያ እና የአስተዳደር መሳሪያ ሆኖ ማገልገል፤በአንድ የዕቅድ ዘመን መንግሥት የሚኖረውን ገቢና ወጪ ማመላከት ፤የመንግሥት የፊስካልና ሞኒተሪ ፖሊሲዎች ለማስፈፀሚያነት ማገልገል ፤ ገቢን በማስፋትና በወጪ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ የዕድገት ቁልፍ መሣሪያ መሆን ፤የልማት ዕቅድን በማስፈጸም ኢኮኖሚ ዕድገት ማምጣት ፤የመንግሥት ስትራቴጂዎቹን፣ ፖሊሲዎቹንና የልማት ዕቅዱችን ማስፈጸም ፤ በአንድ የበጀት ዓመት ስለ መንግስት ገቢና ወጪ የሚተነበይበት ሰነድ ሆኖ ማገልገል እና ሁሉም የመንግስት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ከተሰጣቸዉ ተግባርና ሃላፊነት አንጻር ሊያሳኩ ያስቀመጡትን ዓላማ እንዴትና በምን ያህል ሀብት እንደሚያከናዉኑ የማሳያ ሰነድ ሆኖ ማገልገል የበጀት የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን የሰጡት በትምህርት ሚኒስቴር የዕቅድ እና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን መሪ ዶ/ር ደመላሽ ምስጋና አብራርተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የበጀት ሂደት ከማዕከላዊ መንግስት እስከ ታችኛዉ አስተዳደራዊ የስልጣንን እርከን ድረስ በተመሳሳይ አራት ደረጃዎች በሆኑት የበጀት ዝግጅት፣ በጀት ማጸደቅ፣ በጀት ስራ ላይ ማዋልና በጀት ቁጥጥር ነው ያሉት ዶ/ር ደመላሽ የዜሮ መሠረት ፤የዝርዝር የወጪ አርዕስት ፤የፕሮግራም ፤ፐርፎርማንስ እና የሥርዓተ ፆታ ምላሽ ሰጪ አምስቱ የበጀት ሥርዓቶች መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕሮግራም በጀት ውጤት ላይ ያተኮረ፤ከመስሪያቤቱ ራእይና ተልዕኮ እንዲሁም ከስትራቴጂክ ዕቅድ የሚነሳ፤የልማትእቅድንና በጀትን የሚያገናኝ ፤የመደበኛና ካፒታል ወጪዎችን የሚያቀናጅ፤ለመስሪያ ቤት ነጻነትን በመስጠት ሃላፊነትንና ተጠያቂነትን የሚያስፍን ፤ለክዋኔ ኦዲት መሠረት የሚጥል እና በጀቱ ያስገኘውን ውጤት እና የግብ ስኬት ለመለካት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። በበጀት አጠቃቀም እና አስተዳደር ዙሪያ የትምህርት ሚኒስቴር ተሞክሮ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።በውይይቱ ለተነሱት ሐሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች በአሰልጣኙ በዶ/ር ደመላሽ ምላሸ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የግንዛቤ መስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቋል። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።