ከኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶችን በተመለከተ የተሰጠ ማሳሰቢያ
በቅድመ-ምረቃ እና በድህረ-ምረቃ መርሃ-ግብር ተመዝጋቢዎች የሚከተሉትን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡- ** የትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያሳውቀውን የከፍተኛ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ መግቢያ መስፈርት የመቁረጫ ነጥብ አሟልተው መገኘት አለባቸው፤ ** ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የተመረቁ ባለሙያዎች በከፍተኛ ትምህርት በቅድመ-ምረቃ ደረጃ ለመመዝገብ በሠለጠኑበት የሙያ መስክ በደረጃ 4 ወይንም በቀድሞ 10+3 ወይንም 12+2 ዲፕሎማ ያጠናቀቁ ሆነው በሙያው ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC level 4) ተፈትነው ያለፉበትን ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ ** ለ2ኛ ዲግሪ ተመዝጋቢዎች በባለሥልጣኑ ህጋዊነቱ የተረጋገጠ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፤ እንዲሁም National Graduate Admission Test (NGAT) የማለፊያ ውጤት ያላቸው መሆን አለባቸው ፡፡ ** ከውጭ ሀገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ለመግቢያ መስፈርት የሚያገለግለው በባለስልጣኑ የአቻ ግምት ሲሰራለት ብቻ ይሆናል፡፡ ** ከተጠቀሱ መመሪያዎች ውጪ ገብተው ለሚማሩ ኃላፊነቱ የተመዝጋቢዎቹ እና የተቋማቱ ብቻ መሆኑን እናሳስባለን። የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
