በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የተከለከሉ እና የእርምት እርምጃ የሚያስከትሉ ተግባራት
** ከባለሥልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ ሲያስተምር የተገኘ አዲስ ተቋም፤ ** ፈቃድ ባልተገኘበት ካምፓስ ወይም ቅርንጫፍ ትምህርት ሲሰጥ የተገኘ ተቋም፤ **ባልተፈቀደ የትምህርት-መስክ እና መረሀ-ግብር ትምህርት እየሰጠ የተገኘ ተቋም፤ ** ፍቃድ ሳያድስ ስያስተምር የተገኘ ተቋም፤ ** ከባለሥልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ የህንጻ ለውጥ ያደረገ ተቋም፤ ** የአጫጭር ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት ፈቃድ ሳይሰጣቸው የሚሰሩ ተቋማት ወይም የሙያ ማህበራት፤ ** በባለሥልጣኑ ከተሰጠው የደረጃ ስያሜ ውጪ ሌላ የደረጃ ስያሜ ሲጠቀም የተገኘ ተቋም፣ ** አሳሳች ማስታወቂያ ያሰራጨ ተቋም፤ ** የከፍተኛ ትምህርት የመግቢያ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር የተገኘ ተቋም፤ ** በባለሥልጣኑ ተገምግሞ ያገኘውን ስርዓተ ትምህርት ሳይከተል ትምህርት የሰጠ ተቋም፤ ** የመምህራንን ቁጥር እና ደረጃ አጓድሎና ቀይሮ የተገኘ ተቋም፤ ** በባለስልጣኑ ከተፈቀደው ቁጥር በላይ መዝግቦ ሲያስተምር የተገኘ ተቋም፤ ** የተማሪ መረጃ አያያዝ፣ አጠባበቅና አላላክ፤ ባለሥልጣኑ የተሰጠውን የፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት ደብዳቤ በግልጽ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ በሚታይ ሁኔታ ያለጠፈ ወይም ያላሳወቀ ተቋም እና ** ግብአቶችን አጓድሎ ወይም ከተቋም ወደ ሌላ ተቋም ወይም ካምፓስ አዛውሮ የተገኘ ተቋም፤ሐሰተኛ ሰነዶች እና ትክክለኛ ያልሆኑ ማስረጃዎች ትክክለኛ አድርጎ ማቅረብ ናቸው፡፡ የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
