የሲቪል ሰርቪስ የተቀናጀ መረጃ አያያዝ ሥርዓትን (ICSMIS) ለመተግበር የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ
ጳጉሜ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ለኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ ሥርዓትን (ICSMIS)ለመተግበር የሚያስችል ስልጠና በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተሰጠ። ስልጠናውን የሰጡት በባለስልጣኑ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኔኬሽን የዊብሳይት እና የፖርታል ባለሙያ አቶ አበባው አማረ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስን ዕውን ለማድረግ ከሚያስችሉ የትኩረት ምሰሶዎች አንዱ የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ ሥርዓት(ICSMIS) እንደሆነ ገልጸው ICSMIS Web Based System ሲሆን የፌዴራልና የክልሎችን የሥራ ቋንቋ መሠረት አድርጎ የለማ ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ በመንግሥት ተቋማት በሥራ ላይ ያለውን የሰው ሀይል መረጃ አደረጃጀት እና የአሰራር ሥርዓት(የአገልግሎት አሰጣጥ) እንዲሁም ከተቋማት ጋር የሚደረገውን የመረጃ ልውውጥ ለማዘመን የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሲስተሙ የተለያዩ ዕረፍቶች መጠየቅና ማፅደቅ፣ የዕረፍትና የቅጥር ዳሽቦርዶች፣ የወሰዱት ዕረፍት ሳይጨርሱ ወደ ስራ የሚመለሱ ሠራተኞች የዕረፍት ማስተካከያዎች ማከናወን፣ የግል ታሪክ ማየት፣ የቅጥር መደብ መጠየቅና የቅጥር ሂደቱን ማከናወንና መከታተል፣ የሥራ ልምድ፣ የዋስትና ደብዳቤ እና ሌሎች የድጋፍ ደብዳቤዎች መጠየቅና መስጠት፣ አቤቱታና ጥቆማ ማቅረብ፤ ይግባኝ መክፈትና መከታተል፣ ከተለያዩ ተቋማት የተላኩ ደብዳቤዎች መከታተልና ማስተናገድ፣ እንዲሁም ለማኔጅመንት ውሳኔ የሚያገለግሉ የተለያዩ ሪፖርቶችን ማሳየት እና መጠቀም የሚያስችል ስርዓት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
