በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒኪና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/2016 መሰረት፡-
ፈቃድ ፡- በትምህርት ስልጠና ዘርፍ ለሚሰማራ ተቋማት ተሚሰጥ የትምህርትና ስልጠና የሥራ ምዝገባ ነው። የፈቃድ ዕድሳት፡- ቀደም ሲል በባለሥልጣኑ ፈቃድ የተሰጠው ተቋም የፈቃድ ጊዜው ሲጠናቀቅ ሥራውን እንዲቀጥል የሚሰጥ ፈቃድ ነው። ፈቃድ መሰረዝ ፡- ማንኛውም ተቋም ወይም ፕሮግራም በተሰጠው ፈቃድ መሠረት መስፈርቱን አጓድሎ ሲገኝና በባለሥልጣኑ ሲረጋገጥ በዚህ መመሪያ መሠረት ፈቃድ እንዲመልስ ማድረግ ወይም መንጠቅ ነው ። ዝቅተኛ መስፈርት፡- ማንኛውም ተቋም ፈቃድ ለማግኝት ሊያሟላቸው የሚጠበቁ ባለሥልጣኑ የሚያወጣቸው አነስተኛ የትምህርት ጥራት መለኪያዎች ናቸው። ፈቃድ የሚሰጥበት ዘርፍ፡- **በከፍተኛ ትምህርት ለሚሰማራ ፣አጫጭር ስልጠና ለሚሰጥ ፤ በከፍተኛ ትምህርት የማማከር አገልግሎት የሚሰራ፤ በከፍተኛ ትምህርት ላይ የሙያ ብቃት ምዘና የሚሰጥ እና የፕሮግራም እውና ለሚሰጥ ተቋም ወደ ሥራ እንዲሰማራ የሚሰጥ ፈቃድ ነው። **በፌደራል መንግስት ወይም በውጭ ሀገር ባለሀብት ወይም በሀገር ውስጥ በፌደራል ደረጃ ለመሰማራት የተቋቋመ ወይም በውጭ ሀገር ህግ ተቋቁሞ ስልጠና ለሚሰጥ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም የሚሰጥ ፈቃድ ነው፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::