የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች የባለሥልጣኑን የ2017 በጀት ዓመት የ6ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ገመገሙ
በባለሥልጣኑ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት በወ/ሪት አመለወርቅ ደሳለኝ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል:: በሪፖርቱ በግማሽ ዓመት በባለሥልጣኑ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች፤ ያጋጠሙ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦች እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ሊከናወኑ የሚገቡ የትኩረት አቅጣጫዎች የቀረቡ ሲሆን የዳግም ምዝገባ ስራ እና መረጃ የማጠራት ሥራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ የነበረ እና በቀጣይም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ ያልተካተቱ ነጥቦች ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተነስተው በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው፤የእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ፤በተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ እና የጥራት ኦዲት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ እና በተቋማት ቁጥጥር ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው የውይይት መድረኩን ሲያጠቃልሉ እንዳሉት ባለፉት 6 ወራት የታዩት ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና ያጋጠሙ ችግሮች እንዳይደገሙ በማድረግ ቀጣይ ስራዎችን በፍጥነት፣ በጥራት እና በጥንቃቄ በመስራት ባለሥልጣኑ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ርብርብና ጥረት መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል:: በተጨማሪም የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ መረሀ ግብርን የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ በባለሥልጣኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኔኬሽን ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት በወ/ሮ ትግስት ኮርሳ ቀርቧል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ