በከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የጥራት ኦዲት መመሪያ እና ስታንዳርድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ
ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያን ስካይላይት ሆቴል ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የጥራት ኦዲት መመሪያ እና ስታንዳርዶች ላይ ውይይት ተካሂዷል ። የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ የውይይት መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንዳሉት ት መመሪያና ስታንዳርዶቹ የሀገራችን የልማት እና የእድገት ራዕይ እውን ለማድረግ የሚያስችል በቂ ዕውቀትና ክህሎት ያላቸው ወጣቶችን ለማፍራት በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ መመሪያ እና ስታንዳር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የትምህርት ተቋማትም መመሪያው ከጸደቀ በኋላ በአዲሱ መመሪያ እና ስታንዳርዶች መሠረት አፈጻጸማቸው የሚመዘን መሆኑን ተገንዝበው ከወዲሁ አዲሱን መመሪያ መሠረት አድርገው ዝግጅት ሊያደርጉ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ