ለባለሥልጣኑ ሰራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥ ፣በተገልጋዮች ቅሬታና አቤቱታ አፈታት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጠን ሰራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥ ፣በተገልጋዮች ቅሬታና አቤቱታ አፈታት ላይ ህዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት በባለሥላጣኑ የተቋማዊ ለውጥ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አልማዝ ዱካሞ እንደተናገሩት፤ እኛ ስራ እንድንሰራ የተቀጠርነው ተገልጋዮች ስላሉ ነውና ተገልጋዮቻችንን በትህትና እና በክብር ማስተናገድ ይገባናል ብለዋል፡፡በቀጣይም በየዘርፍ ያሉ ሰራተኞች ተገልጋዮችን በቅንነት፣ በታማኝነትና በሀላፊነት መንፈስ ቀልጣፋ አገልግሎት ሊሰጡ እንደሚገባ አሳስበዋል። ስልጠናውን የሰጡት ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽንና ምዝገባ ዴስክ ተ/ኃላፊ አቶ መሐመድ ሰይድ በአገልግሎት አሰጣጥ ፣በተገልጋዮች ቅሬታና አቤቱታ አፈታት የሚመለከት መነሻ ጽሁፍ አቅርበው ተቋሙ ከተቋቋመበት ዓላማ አንጻር የስራ ክፍሎች ተገልጋዮቻቸውን እንዴትና በምን ሁኔታ ማስተናገድ እንደሚገባ የሌሎች ተቋማትን ልምድ በመጥቀስ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡አቶ መሐመድ ከዚህ ጋር አያይዘው በቀጣይ የዜጎች ቻርተር ተዘጋጅቶ የተሟላ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ ላይ የተመሰረተ አገልግሎት ተግባረዊ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ በዕለቱ በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ ከሰራተኞች ጥያቄዎችና አስተያይቶች ተነስተው መልስና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
