ለባለሥልጣኑ መካከለኛ አመራሮች በእቅድ አስተቃቀድ እና በአፈጻጸም ሪፖርት አዘገጃጀት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
ለባለሥልጣኑ መካከለኛ አመራሮች በእቅድ አስተቃቀድ እና በአፈጻጸም ሪፖርት አዘገጃጀት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ ከህዳር 14 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ በእቅድ አስተቃቀድ እና በአፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ለባለሥልጣኑን መካከለኛ አመራሮችን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ታደሰ እቅድ እና የአፈጻጸም ሪፖርት ሥራ በባለሥልጣኑ ለሚከናወኑ ሁሉም ሥራዎች መሠረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኢፌዲሪ የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አቶ ታምሩ ተረፈ ስለ እቅድ ምንነት፣ስለእቅድ ዓይነቶች፣ ስለውጤታማ እቅድ አስተቃቀድ፣ ስለ ሪፖርት አዘገጃጀት፣ ስለ ሪፖርት መሠረታዊ ይዘቶች እና ስለ ሪፖርት አቀራረብ በሰፊው አብራርተዋል፡፡ በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ