ለውጭ ተባባሪ ገምጋሚዎች በፈቃድ አሰጣጥ እና በዳግም ምዝገባ መምሪያ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ለውጭ ተባባሪ ገምጋሚዎች የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባን መሠረት አድርጎ በፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተሰጠ፡፡ የፈቃድ መመሪያ፣ መስፈርት እና የዳግም ምዝገባ መምሪያ የከፍተኛ ትምህርት ፍቃድ አሰጣጥ መሪ ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት ወ/ሮ ሂይወት አሰፋ፤ ለከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ እና የፈቃድ እድሳት አሰጣጥ ለውጭ ተባባሪ ገምገሚዎች የተዘጋጀ የስምምነት ውል በባለሥልጣኑ የከፍተኛ ትምህርት ፍቃድ አሰጣጥ የዴስክ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ታምሩ መስፍን እና የከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ እና የፈቃድ እድሳት አሰጣጥ ቼክ ሌስት የከፍተኛ ትምህርት ፍቃድ አሰጣጥ የዴስክ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ጀምበሩ አለማየሁ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የከፍተኛ ትምህርት ፍቃድ አሰጣጥ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሂይወት አሰፋ ፤ በአቶ ታምሩ መስፍን እና በአቶ ጀምበሩ አለማየሁ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በስልጠና መረሀ ግብሩ መጨረሻ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዝናቡ ሀምሳሉ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በአዋጅ የተሰጠውን የትምህርትና ስልጠና ጥራትን የማረጋገጥ ተልዕኮ ለማሳካት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው በስልጠናው የተገኙ የውጭ ገምጋሚ ባለሙያዎች(External assessors) ከባለሥልጣኑ ጋር ሆነው የማይተካ ድርሻቸውን እንዲወጡ ከአደራ ጭምር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ