ማሳሰቢያ

በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም የተጀመረው የዳግም ምዝገባ ሥራ የመጀመሪያ ዙር ነገ ቅዳሜ መስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም የምናጠናቅቅ እና ሁለተኛ ሳምንት የዳግም ምዝገባ ሥራ ሰኞ መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቀጥል መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በዚህ ሊንክ http://bit.ly/4do4ZUJ በተገለጸላችሁ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በባለስልጣኑ ቅጥር ግቢ በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በዳግም ምዝገባ ሂደት ውስጥ ያልገባ ተቋም መምሪያው ላይ በተቀመጠው አንቀጽ 2(11)መሠረት ከባለሥልጣኑ የወሰደው የማስተማር ፈቃድ በገዛ ፈቃዱ እንዳቋረጠ ተቆጥሮ ፈቃዱ የሚነጠቅ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ