ለባለሥልጣኑን መካከለኛ አመራሮች የተግባቦት አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ
መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ የተግባቦት ክህሎት ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ተልእኮ መሳካት በሚል ርዕስ ለባለሥልጣኑን መካከለኛ አመራሮችን የተግባቦት አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ፡፡ የሥልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዝናቡ ሀምሳሉ የኮሙዩኔኬሽን ሥራ በባለሥልጣኑ የሚከናወኑ ሁሉም ሥራዎች ሊታወቁ የሚችሉት በጠንካራ የኮሙዩኔኬሽን ሥራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙትና ኮሙዩኔኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ማርታ አድማሱ በበኩላቸው የባለሥልጣኑን የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኔኬሽ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚያከናውናቸው አበይት ተግባራት አንዱ የባለሥልጣኑን አመራሮች የኮሙዩኔኬሽን ወይም የተግባቦት አቅም ማጎልበት እና ማሳደግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኢፌዲሪ የመንግስት ኮሙዩኔኬሽን አገልግሎት የኹነትና ሕዝባዊ መድረክ ዝግጅት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም በዕውቀት ስለ ተግባቦት ምንነት፣ስለተግባቦት ዓይነቶች፣ስለተግባቦት ጥቅሞች፣ስለውጤታማ ተግባቦት፣ስለተግባቦት ወሳኞች፣ስለተቋማዊ ተግባቦት ባለቤት ማንነት፣ ስለተግባቦት ባለሙያ ተግባራት፣ስለየሚዲያ ተቋማት ሚና፣በመልካም ሥነ ምግባር የተገነባ ኅብረተሰብ ስለመፍጠር እና የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን ስለማጠናከር በሰፊው አብራርተዋል፡፡ በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ