በ2016 በጀት ዓመት የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው ተገለጸ

የትምህርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እና የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስ (ሳይንስ ፋክሌቴ) መሰብሰቢያ አዳራሽ የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን በጋራ በገመገሙበት ወቅት እንደተገለጸው የትምህረትን ጥራት ለማስጠበቅ፣የትምህርት ተደራሽነት እና የትምህርት አሳታፊነትን ለማሳደግ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል፡፡ በመድረኩ ላይ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች፤ ያጋጠሙ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦች እንዲሁም በቀጣይ ሊከናወኑ የታቀዱ ሥራዎች ቀርበዋል፡፡ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ያቀረቡት የባለስልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዝናቡ ሀምሳሉ የከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ እና የትምህርት ማስረጃዎች ማረጋገጥና የአቻ ግመታ አገልግሎት በበይነ መረብ ጥያቄ ማቅረብ የተቻለበት ፤ለባለስልጣኑ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎች እና ስታንዳርዶች ጸድቀው ስራ ላይ የዋሉበት እና የባለስልጣኑን አሰራር በማዘመንና ከብልሹ አሰራር በማላቀቅ ረገድ በርካታ ተግባራት በበጀት ዓመቱ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር ዘርፍ፣የአጠቃላይ ትምህርት እና የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ እቅድ አፈጻጸም ፤ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም፤ እና የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎትየ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች እንዲሁም የትምህርት ሴክተር ሪፎርም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተነስተው በትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ