ማስታወቂያ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፦ የተመራቂ ተማሪዎችን ዝርዘር መረጃ መላኪያ ቅፅ ለውጥ ስለማሳወቅ፤

ከባለስልጣኑ ፈቃድ የተሰጣቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከዚህ በፊት ያላካችሁትን የተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ እና በ2015 ዓ.ም፣ 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ያለፉ ብቻ ከዚህ በፊት በተላከው ቅጽ መሰረት ዝርዝር መረጃውን እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንድትልኩ ለመጨረሻ ጊዜ ብለን በቀን ሰኔ 10/2016 ዓ.ም በቁጥር 11/77/868/16 በወጣው ደብዳቤ ማሳወቃችን ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን የመላኪያ ቅጹ ይዘት ለትምህርትና ማስረጃ ማረጋገጥ የስራ ክፍል ለሚጠቀምበት ሲስተም አመቺ ይሆን ዘንድ ቅጹ ላይ ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ከዚህ ደብዳቤ ጋራ አባሪ አድርገን በላክነው ቅፅ በመጠቀም ዝርዝር መረጃውን እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንድትልኩ ለመጨረሻ ጊዜ እናሳስባለን፡፡ በፊስቡክ -hFDRE Education and Training Authority-ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ