የባለሥልጣኑ የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

የባለሥልጣኑ የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ ------------------------------------------------------------------------ ከሚያዚያ 8 እስከ 9 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው አዜማን ሆቴል ባለፉት ዘጠኝ ወራት በባለሥልጣኑ ሊሰሩ የታቀዱ ዋና ዋና ግቦችን መነሻ በማድረግ በየሥራ ክፍሎቹ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበው ውይይት እና ግምገማ ተደርጎባቸዋል:: በግምገማ መድረኩ የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥና የጥራት ኦዲት፤ የእውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን ፤የተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ፤የሥራ አመራር እና የአስተዳደር ዘርፎች በዘጠኝ ወራት ሊሰሯቸው የታቀዱ ዋና ዋና ግቦችን መነሻ በማድረግ በየሥራ ክፍሎቹ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር በየሥራ ክፍሉ ኃላፊዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል:: ባለሥልጣኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ ውጤታማ ተግባራትን እንዳከናወነ የተገመገመ ሲሆን በተለይም በፈቃድ አሰጣጥና የጥራት ኦዲት ዘርፍ በአዲስ አበባ የሚገኙ የግል ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ እንዲያልፉ መደረጉ ፤ የዳግም ምዝገባ ውሳኔ የያዘ ሪፖርት ለተቋማቱ እንዲደርስ መደረጉ ፤ በክልል የሚገኙ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ ፤ ለክልል መንግስታት ተጠሪ የሆኑ ተቋማት በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ ፤ በፌደራል ደረጃ የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እና በዳግም ምዝገባ ውሳኔ ቅሬታ ላቀረቡ ተቋማት ምላሽ መሰጠቱ እና ለብቃት ፈቃድ ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠቱ ፤ የጥራት ኦዲት ሥራን አስመልክቶ በፕሮግራም የጥራት ኦዲት ስታንዳርድ መሠረት ተቋማት ግለ ግምገማ እያካሄዱ መሆኑን፤በአስር የከፍተኛእና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የጥራት ኦዲት እየተከናወነ መሆኑ እና ለዘጠና ሰባት የጥራት ኦዲተሮች ስልጠና የተሰጠ መሆኑ እና የአጠቃላይ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ ላይ የተሠሩ ሥራዎች አፈጻጸም ያደገ መሆኑ፤ በእውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ስለእውቅና አሰጣጥ ያለው ግንዛቤ መዳበሩ፣በርካታ ተቋማት የፕሮግራም እውቅና ይሰጠን የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው እና ለሁለት ፕሮግራሞች ሙሉ እውቅና ለአምስት ዓመት ለስድስት ፕሮግራሞች ደግሞ በቅድመ ሁኔታ ለሶስት ዓመት እውቅና መሰጠቱ፤እንዲሁም በባለሥልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ስራ ክፍል የናሚቢያ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ካውንስል (NCHE) ተሞክር መወሰድ መቻሉ፤በኢትዮጵያ ሰባተኛው የትምህርት ሴክተር ልማት ፕሮግራም ( ESDP VII-2019-2023 ዓ.ም) ሪፖርት ዝግጅት ላይ ተሳትፎ ማድረግ መቻሉ፤ በተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ዘርፍ የተቋማት የክትትልና ቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ እና የኢንስፔክሽን ስራ አፈጻጸም ጥሩ ደረጃ ላይ ያለ መሆኑ እንዲሁም የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ አገልግሎት አሰጣጥን መሻሻል በመቻሉ ከበርካታ የመንግስት እና የግል ተቋማት የሠራተኞቻችን የትምህርት ማስረጃ ይረጋገጥልን ጥያቄ መቅረቡ እና በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው በግል የራስን ትምህርት ማስረጃ የማረጋገጥ ፍላጎትና ተነሳሽነት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ እንዲሁም ባለሥልጣኑ ከመሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ለበርካታ የትምህርት ማስረጃዎች ማረጋገጫ የሰጠና እና የአቻ ግመታ ሥራ ያከናወነ መሆኑ፤ በሥራ አመራር እና በአስተዳደር ዘርፉም የተቋሙ ዋና ዋና ዘርፎች በመደገፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል የተሠሩ ሥራዎች ጥሩ አፈጻጸም ላይ መሆናቸው ፤ የባለሥልጣኑን ተቀባይነት ከፍ ለማድረግ የሚያስችለው የውስጥ ጥራት ኦዲት ስራ ከኢትዮጵያ ስታንዳር ኢንስቲትዩት ጋር በጥራት አስተዳደር ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የቴክኒክ ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሞ ወደ ሥራ መገባቱ እና ለማኔጅመንትና ዓለም አቀፍ የጥራት አመራር ስርዓት ISO9001:2015 ለመተግበር ለተቋቋመው ግብረ ሀይል ስልጠና መሰጠቱ በውይይቱ እና በግምገማ መድረኩ ከታዩት መካከል ይጠቀሳሉ:: የግምገማ መድረኩን የመሩት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው መድረኩ ያለፉት ሥራዎች የተገመገሙበት ፤የቀሩ ሥራዎች የሚከናወኑበት እና ለቀጣይ በጀት ዓመት የሚሆን እቅድ የሚዘጋጅበት መሆኑን ገልጸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባለሥልጣኑ የእቅዱ ዘጠና ከመቶ ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል፡፡ በግምገማ መድረኩ ከባለሥልጠኑ ዋና ዳይሬክተር እስከ ቡድን መሪዎች ድረስ የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል:: የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ ።