በኢፊዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የስታንደርዳይዜሽንና ጥናትና ምርምር ስራ ክፍል ለትምህርት እና ስልጠና ጥራት የተመረጡ የጥናትና ምርምር ርዕሰ ጉዳዮች

#በኢፊዲሪ_የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን #የስታንደርዳይዜሽንና_ጥናትና_ምርምር_ስራ_ክፍል #ለትምህርት_እና_ስልጠና_ጥራት_የተመረጡ_የጥናትና_ምርምር_ርዕሰ_ጉዳዮች #1_መግቢያ የኢፊዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የትምህርትና ስልጠና ጥራትን የሚደግፉ ሳይንሳዊ ምርምሮችን እንዲያካሂድ በደንብ ቁጥር 515/2022 አንቀፅ 9 ስልጣን ተሰጥቶታል። ይህም የጥራት ማረጋገጫ ውሳኔዎች በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን ያረጋግጣል። የጥናትና ምርምር ስራዎችን ለመከውን ደግሞ በቅድሚያ የትኩረት መስኮች (Thematic areas) መለየት አለባቸው። ይህ ልየታ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም ፣ተጨባጭ ተፅእኖ ለመፍጠር፣ በተቋሙ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ጉዳዮች ቅድሚያ ለመስጠት እና ከሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ጋር ለማጣጣም ወሳኝ ሚና አለው፡፡ በዚህ መሠረት በባለሥልጣኑ የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ሥራዎች በሚከተሉት ዐበይት እና ንዑሳን ዐበይት የትኩረት መስኮች ላይ የሚያጠነጥኑ እንዲሆኑ በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ተመርጠዋል፡፡ #II_ዐበይት_እና_ንዑሳን_ዐበይት_የጥናትና_ምርምር_መስኮች #1_ዓለም_አቀፍ_የጥራት_ማረጋገጫ_ማዕቀፎርች_ፖሊሲዎች_እና_አስተዳደር 1.1. አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ የጥራት ማዕቀፎች ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር መጣጣም 1.2. የአካዳሚክ እውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን፤ 1.3. የአካዳሚክ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ኦዲት፣ ክትትል፡ ቁጥጥር እና እንስፔክሽን፤ 1.4. የውስጥ እና የውጭ የጥራት ማረጋገጫ ስርዓቶች፤ 1.5. በጥራት ማረጋገጥ ስራ ውስጥ የነጻና ገለልተኛነት እና ተጠያቂነት ጉዳይ ፤ 1.6. የጥራት ማረጋገጫ ፖሊሲ ዝግጅት እና ትግበራ፤ 1.7. ድንበር ተሻጋሪ እና ዓለም አቀፍ የጥራት ማረጋገጫ ፈተናዎች፤ 1.8. የዲጂታል እና የቅይጥ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጫ ፤ 1.9. የጥራት ማረጋገጫ ሥርዓቶች እና የአመራር እና ለውጥ አስተዳደር፤እና 1.10. የአስተዳደር ሞዴሎች የጥራት ባህልን ለማሳደግ ናቸው። #2_ስታንዳርዶች_ስርዓተ_ትምህርት_ፔዳጎጂ_እና_ምዘና 2.1. ከዓለም አቀፍ፣ ቀጠናዊ እና ኢንዱስትሪ ስታንዳርዶች ተሞክሮ አንጻር ማየት፤ 2.2. የፕሮግራም ፍላጎቶ ዳሰሳ፤ 2.3. የሥርዓተ ትምህርት ከብሔራዊ የብቃት ማዕቀፎች (NQFs) እና እየተፈጠሩ ካሉ ውጤት ወይም ብቃት ተኮር ሞዴሎች ጋር መጣጣም 2.4. የስርዓተ ትምህርት አግባብነት እና ፈጠራዊነት፤ 2.5. የስርዓተ ትምህርት ቀረጻ፣ ትግበራ እና ግምገማ፤ 2.6. የሀገር በቀል ዕውቀትን በስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ ማዋሃድ፤ 2.7. ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ እና ፈጠራ የታከለበት የመማር ማስተማር ሂደት/አቀራረብ/ 2.8. የአጫጭር ትምህርትና ስልጠናዎች ማስረጃዎች እና ዲጂታል ባጆች ውህደት፤ 2.9. የተማሪዎች ተሳትፎ እና እርካታ ምዘና ፤እና 2.10. የመምህራን ብቃት እና ሙያዊ ዕድገት ናቸው። #3_የግምገማ_እና_የምዘና_ዘዴዎች 3.1. የምዘና አሰራሮች ጥራት እና ትክክለኛነት፤ 3.2. የክትትልና ፈጣን ግብረ መልስ እና የማጠቃለያ ምዘናዎች አጠቃቀም ፤ 3.3. የትምህርት ውጤት፥ብቃትና የምዘና መስፈርት፤ 3.4. የተመራቂዎችን የስራ እድል መለካት፤እና 3.5. ስለቅድመ ትምህርት እውቅና ናቸው። #4_በጥራት_ማረጋገጥ_ሂደት_ውስጥ_ዲጂታላይዜሽን_ፈጠራ_እና_ቴክኖሎጂ 4.1. የጥራት ማረጋገጫ ስርዓት ለበይነ መረብ፣ለርቀት እና ለቅይጥ ትምህርትና ለዲጂታል ማስረጃዎች ፤ 4.2. የአርትፊሻል ኢንተለጀንስ እና ማሽን ለርኒንግ ሚና በትምህርት ጥራት ቁጥጥር፤ 4.3. የጥራት ማረጋገጫን የሚያግዙ ዲጂታል ዘዴዎች እና መሳሪያዎች፤ 4.4. ያልተማከለ እና ዲጂታል የትምህርትና ስልጠና ማስረጃ ማረጋገጫ ሥርዓቶች፤ 4.5. የሳይበር ደህንነት፣ የመረጃ ግላዊነት እና የመረጃ ደህንነት ጥበቃ ስነምግባር፤እና 4.6. የዲጂታል ክህሎቶች እድገት ለጥራት ማረጋገጫ ተዋናዮች ናቸው። #5_ምርምር_ማስረጃ_እና_የጥራት_ማረጋገጫ_ፈጠራ 5.1. የምርምር ውጤቶች ለትምህርት ጥራት መሻሻል 5.2. ለጥራት ማረጋገጫ ለማሻሻል የጥናትና ምርምር ሚና 5.3. የጥናትና ምርምር የገንዘብ ድጋፍ እና አስተዳደር፤ 5.4. የጥራት ማረጋገጫ ፤በትምህርት ውጤቶች እና በስራ ዕድል ላይ ያለው ተጽዕኖ ግምገማ 5.5. የጥራት ማረጋገጫ በፈጠራ፣በተቋም ገጽታ እና ደረጃ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ፤ 5.6. አዳዲስ የጥራት ማረጋገጫ ሞዴሎች፣ ቴክኖሎጂዎች እና አቀራረቦችን መሞከር/መለማመድ ናቸው። #6_ዘላቂነት_አረንጓዴ_ክህሎት_እና_ማህበራዊ_ሃላፊነት 6.1. ዘላቂነትን እና ዘላቂ የልማት ግቦችን በጥራት ማረጋገጫ ውስጥ ማካተት፤ 6.2. ተከታታይት ያለው የጥራት መሻሻል ባህልን ማሳደግ፤እና 6.3. ማህበራዊ ሃላፊነት የሚሰማቸው እና ዘላቂነት ያላቸውን ተመራቂዎ በማፍራት ላይ የጥራት ማረጋገጫ ሚና ናቸው። #7_ስነምግባር_ታማኝነት_እና_ሙያዊነት_ለጥራት_ማረጋገጫ_ያለው_ሚና 7.1. ሙያዊ ስነምግባር እና ቁርጠኝነት፤ 7.2. የአመራር ስነምግባር እና ኃላፊነት፤ 7.3. የባለድርሻ አካላት ስነ ምግባር እና ተጠያቂነት፤እና 7.4. በጥራት ማረጋገጫ ሂደቶች እና ግምገማዎች ውስጥ የአካዳሚክ ታማኝነት ሚና ናቸው። #8_የሰው_ሀይል_የገበያ_አግባብነት_የስራ_እድል_እና_አጋርነት 8.1. የቀጣሪዎች እና የኢንዱስትሪ ተሳትፎ በስርዓተ ትምህርት እና የጥራት ማረጋገጫ፤ 8.2. ሥራ ተኮር ትምህርት፣ ልምምድ እና የዕድሜ ልክ ትምህርት፤ 8.3. የመከታተያ ጥናቶች እና የሰው ሀይል ገበያ ምላሽ ሰጪነት፤ 8.4. የወደፊት ችሎታ ትንበያ (አረንጓዴ እና ዲጂታል ኢኮኖሚዎችን ጨምሮ)፤እና 8.5. የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ሽርክና፤ የአሠሪዎች፤ የሙያ ማህበራት እና ዓለም አቀፍና ቀጠናዊ ትብብር ናቸው። #9_የአቅም_ግንባታ_እና_ሙያዊ_እድገት 9.1. የጥራት አረጋጋጭ ባለሙያዎች፣ የተቋማት መሪዎች እና ምሁራን ስልጠና እና ልማት፤እና 9.2. ዓለም አቀፍ ትብብር፣ የአቻ ትምህርት እና የትግበራ ማህበረሰብ ናቸው። የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ