ቢንግሀም አለም አቀፍ ትምህርት ቤት ያቀረበውን የፈቃድ እድሳት ጥያቄ በተመለከተ ከባለሥልጣኑ የተሰጠው ምላሽ
#ለቢንግሀም_አለም_አቀፍ_ትምህርት_ቤት አዲስ አበባ ጉዳዩ፦ትምህርት ቤቱ ያቀረበውን የፈቃድ እድሳት ጥያቄ ይመለከታል -------------------------------------------------------------- ቢንግሀም አለም አቀፍ ትምህርት ቤት የአለም አቀፍ ስርአተ ትምህርት ለማስተማር ይችል ዘንድ ከመስከረም 2014ዓ.ም እስከ ሐምሌ 2017ዓ.ም ፈቃድ የሰጠው መሆኑ ይታወቃል።ይህንን የፈቃድ ጊዜው መጠናቀቅ መሰረት በማድረግ ትምህርት ቤቱም የፈቃድ እድሳት እንዲደረግለት ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር BA/HR/091/25 ጥያቄ አቅርቧል። መስሪያ ቤቱም የገምጋሚ ባለሙያዎች ቡድን በማዋቀር የሰነድ እና የዶክመንት ምርመራ አድርጓል። ነገር ግን በግምገማ ወቅት ለፈቃድ እድሳት የሚያስፈልጉትን አነስተኛ መስፈርቶች ስላልተሟሉ የፈቃድ እድሳት ማድረግ አልተቻለም። በመሆኑም ይህ ደብዳቤ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከትምህርት ቤቱ የሚጠየቁ ከአለም አቀፍ ስርአተ ትምህርት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ጥያቄዎች የማያስተናግዱ መሆኑን እናሳውቃለን።
