የADRI የጥራት ሞዴልን የመጠቀም ጥቅሞች፡-
የADRI የጥራት ሞዴልን የመጠቀም ጥቅሞች፡- ------------------------------------------ ** የመሻሻል ባህልን ይፈጥራል ትኩረትን የጥራት ኦዲት ግምገማን ብቻ ማለፍ ላይ ከማድረግ ወደ በየቀኑ መሻሻል ይለውጣል፤ ** አጠቃላይ እይታን ይሰጣል በዕቅድ፣ በድርጊት፣ በውጤቶች እና በመማር መካከል ያለውን ግንኙነት አጠቃሎ ለማየት ያስችላል፤ ** ለጥራት ኦዲት ሥራ እሴት ይጨምራል የጥራ ኦዲተሮች ሥራን የፖሊስ ሥራ ከመሰለ ተግባር ወደ አማካሪነት እና እሴት ወደ እሚጨምር ግንኙት ያሳድጋል፤ ** የብስለት ደረጃን ለማሳየት ያስችላል ተቋሙ አስቀድሞ የነቃ፣ በማስረጃ ላይ የተመሠረተ እና እራሱን መተች የሚችል መሆኑን ለእውቅና ሰጪዎችን እና ለባለድርሻ አካላት እንዲያሳይ ያደርጋል ፤ እና ** አጠቃላይ የጥራት ኦዲት ሥራ እንቅስቃሴ በጥሩ ሁኔታ እንዲከናወን ወይም እንዲፈጸም ያስችላል በመሻሻል ደረጃ ላይ ያለው ጥረት ከንቱ እንዳይሆን እና በሂደቱ የተገኑ መረጃዎች ትርጉም ላለው ለውጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ ናቸው፡፡
