በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ 991/2016 መሠረት ስለጥራት ክትትል እና ስለእውቅና ማበረታቻዎች

በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ 991/2016 መሠረት ስለጥራት ክትትል እና ስለእውቅና ማበረታቻዎች --------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------- #ስለጥራት_ክትትል ** እውቅና ያገኘ ተቋም ወይም ፕሮግራም እውቅና ሪፖርት ላይ የተገለጹትን የጥራት ጉድለቶችን ስለማሻሻሉ ለማረጋገጥ የሚያስችል የማሻሻያ እቅድ እና ሪፖርት በየዓመቱ ይልካል፤ እና ** በሪፖርቱ መሠረት ባለሥልጣኑ ክትትል ያደርጋል፤ በአካል በመገኘትም ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡ #ስለእውቅና_ማበረታቻዎች #የትምህርት_የሚኒስቴር_እውቅና_ለተሰጣቸው_ተቋማትና_ፕሮግራሞች_የሚከተሉትን_ማበረታቻዎች_ሊሰጥ_ይችላል_፡፡ ** ተማሪን በልዩ ሁኔታ መመደብ፤ ** ለጥናትና ምርምር በልዩ ሁኔታ በጀት መመደብ፤ ** ለተቋሙ መምህራንና ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የትምህርት እድል መስጠት፤ ** ከባለስልጣኑ ጋር በመሆን የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም እውቅና ያላቸውን ተቋማት ወይም ፕሮግራም ማስተዋወቅ፤ እና ** ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ወይም ባለድርሻ አካላት ጋር በልዩ ሁኔታ ትስስር እንዲፈጥሩ ድጋፍ ማድረግ፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።