ለመጀመሪያ_ዲግሪ_የትምህርት_ማስረጃዎች (Bachelor's Degree)፤ ለሁለተኛ ዲግሪ (Master’s Degree) እና ለሦስተኛ_ዲግሪ (PhD Degree) የትምህርት ማስረጃ የአቻ-ግመት ለማሰራት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
#የአቻ_ግመታ_የምስክር_ወረቀት ማለት ከውጭ ሀገር የተገኘ የትምህርትና ስልጠና ማስረጃ በኢትዮጵያ ብቃት ማረጋገጫ ማእቀፍ አውድ ውስጥ ተቃኝቶ አቻ ደረጃ የሚገልጽ በባለሥልጣኑ ለትምህርት ማስረጃ ባለቤት የሚሰጥ ሰነድ ነው፡፡ ***** ***** ***** ***** ***** ****** ***** ***** ***** ***** ****** ****** ***** ***** ***** ****** ****** ***** ***** ***** ****** ***** ***** #ለመጀመሪያ_ዲግሪ_የትምህርት_ማስረጃዎች(Bachelor's Degree) የትምህርት ማስረጃ የአቻ-ግመት ለማሰራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሊሟሉ ይገባል 1. ዲግሪው በተገኘበት ሀገር የውጭጉዳይ ሚነስቴር እና የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የመጀመሪያ ዲግሪ የምስክር ወረቀት እና ትራንስክሪፕት ፤ 2. በተገኘበት ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት/ዲፕሎማ/ (ከውጭ ሀገር የተገኘ ከሆነ ብቻ)፤ 3. በትምህርት ምዘናዎችና ፈተናዎች አገልግሎት ድርጅት ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት ፤ 4. ፓስፖርት እና የተማረበት ሀገር ለትምህርት የገባበት ቪዛ ፤እና 5. የአገልግሎት ክፍያ (225 ብር ለኢትዮጵያዊ/ት እና 450 ኢትዮጵያዊ ላልሆነ/ች) ማሳሰቢያ:- የትምህርት ማስረጃው የተገኘው በሌሎች የውጭ ሀገራት ቋንቋዎች ከሆነ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ አግባብነት ባለው አካል የተረጋገጥ (Sworn translation) ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡ #ለሁለተኛ_ዲግሪ (Master’s Degree) #የትምህርት_ማስረጃ የአቻ-ግመት ለማሰራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሊሟሉ ይገባል:- 1. በተገኘበት ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚነስቴር እና የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የ2ኛ ዲግሪ የምስክር ወረቀት እና ትራንስክሪፕት ፤ 2. የመጀመሪያ ዲግሪ የምስክር ወረቀት እና ትራንስክሪፕት ፤ 3. በተገኘበት ሀገር የውጭጉዳይ ሚነስቴር እና የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የመጀመሪያ ዲግሪ የምስክር ወረቀት እና ትራንስክሪፕት (ከውጭ ሀገር የተገኘ ከሆነ ብቻ)፤ 4. በትምህርት ምዘናዎችና ፈተናዎች አገልግሎት ድርጅት ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የምስክርወረቀት ፤ 5. በተገኘበት ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት/ዲፕሎማ (ከውጭ ሀገር የተገኘ ከሆነ ብቻ) ፤ 6. ፓስፖርት እና የተማረበት ሀገር ለትምህርት የገባበት ቪዛ ፤ እና 7. የአገልግሎትክፍያ (225 ብር ለኢትዮጵያዊ/ት እና 450 ኢትዮጵያዊ ላልሆነ/ች) #ማሳሰቢያ:- የትምህርት ማስረጃው የተገኘው በሌሎች የውጭ ሀገራት ቋንቋዎች ከሆነ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ አግባብነት ባለው አካል የተረጋገጥ (Sworn translation) ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡ #ለሦስተኛ_ዲግሪ (PhD Degree) #የትምህርት_ማስረጃ የአቻ-ግመት ለማሰራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሊሟሉ ይገባል:- 1. በተገኘበት ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚነስቴር እና የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የ3ኛ ዲግሪ የምስክር ወረቀት እና ትራንስክሪፕት ፤ 2. በተገኘበት ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚነስቴር እና የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የ2ኛ ዲግሪ የምስክር ወረቀት እና ትራንስክሪፕት (ከውጭ ሀገር የተገኘ ከሆነ ብቻ)፤ 3. በተገኘበት ሀገር የውጭጉዳይ ሚነስቴር እና የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የመጀመሪያ ዲግሪ የምስክር ወረቀት እና ትራንስክሪፕት ፤(ከውጭ ሀገር የተገኘ ከሆነ ብቻ) 4. በተገኘበት ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት/ዲፕሎማ/ (ከውጭ ሀገር የተገኘ ከሆነ ብቻ) ፤ 5. ፓስፖርት እና የተማረበት ሀገር ለትምህርት የገባበት ቪዛ ፤እና 6. የአገልግሎትክፍያ (225 ብር ለኢትዮጵያዊ/ት እና 450 ኢትዮጵያዊ ላልሆነ/ች) #ማሳሰቢያ:- የትምህርት ማስረጃው የተገኘው በሌሎች የውጭ ሀገራት ቋንቋዎች ከሆነ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ አግባብነት ባለው አካል የተረጋገጥ (Sworn translation) ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡ (የትምህርት ማስረጃ እና የአቻ ግመታ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 990/2016 ክፍል ሶስት የተወሰደ) የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
