ማሳሰቢያ ለሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በያሉበት
#ማሳሰቢያ #ለሁሉም_የመንግስት_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት #በያሉበት በኢፌዲሪ የፌዴራል መንግስት አስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 ዓም አንቀጽ 60፣ በትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን አደረጃጀት ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ ደንብ 515/2014 ዓ/ም አንቀፅ 6(6) ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር እንዲሁም በኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ቁጥር 990/2016 ዓ/ም አንቀፅ 4 እና 10 መሠረት በሀገር ውስጥ የተገኙ የትምህርትና ስልጠና ማስረጃዎችን ያረጋግጣል በውጭ ሀገር የተገኙ የትምህርትና ስልጠና ማስረጃዎችንም አቻ ግመታ ይሰራል። በዚሁ መሠረት በየተቋማቱ የሚገኙ የአካዳሚክ፤የምርምር እንዲሁም የአሰተዳደር ሰራተኞች በሀገር ውስጥ ለተገኘ የትምህርትና ስልጠና ማስረጃ ከግል ተቋማት ለተገኙት ቅድሚያ በመስጠት እንዲያረጋግጡ፤ ከውጭ ሀገር ለተገኘ የትምህርትና ስልጠና ማስረጃ ደግሞ አቻ ግመታ እንዲያሰሩ ይህ ባልሆነበት ግን ማናቸውም የትምህርትና ስልጠና ማስረጃውን ማግኘት ተከትሎ የሚደረግ ውድድር፤ ቅጥር፤ የደረጃ እድገት፤ ወዘተ እና ተያያዥ ጥቅማ ጥቅሞች መፍቀድ እና መስጠት በሚመለከተው አካል እና አግባብነት ባለው ህግ የሚያስጠይቅ መሆኑ ለማሳሰብ እንወዳለን። የተቋማት በየደረጃው ያለው አመራርም ሰራተኞች ለትምህርትና ስልጠና በሚልክበት ጊዜ ሰለማስረጃ ማረጋገጥና አቻ ግመታ ወሳኝነት በቂ መረጀ እንዲኖራቸው ቢያደርግና በየደረጃው ማሟለት ያለባቸውን ጉዳዮች አሟልተው ያለእንግልት እንዲገለገሉ ለማስቻል እገዛ እንዲያደርግ እናሳውቃለን። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
