በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተቋም እና የፕሮግራም አሰጣጥ እውቅና መመሪያ 991/2016 መሠረት የእውቅና አሰጣጥ፤የእውቅና አሰጣጥ ካውንስል ፤ገምጋሚ ባለሙያ፤ተባባሪ (የውጭ) ገምጋሚ ባለሙያ እና አሰልጣኝ ማለት፡-
በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተቋም እና የፕሮግራም አሰጣጥ እውቅና መመሪያ 991/2016 መሠረት የእውቅና አሰጣጥ፤የእውቅና አሰጣጥ ካውንስል ፤ገምጋሚ ባለሙያ፤ተባባሪ (የውጭ) ገምጋሚ ባለሙያ እና አሰልጣኝ ማለት፡- -------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------- ** #የእውቅና_አሰጣጥ ማለት ለተቋምና ለፕሮግራም እውቅና ወይም እውቅና እድሳት ለመስጠት የሚደረግ ሂደትን በሙሉ ያካተተ ነው:: ** #የእውቅና_አሰጣጥ ካውንስል ማለት በዋና ዳይሬክተሩ የሚሰየም፤ የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የሚያጸድቅ አካል ነው:: ** #ገምጋሚ_ባለሙያ ማለት በተቋም እና በፕሮግራም እውቅና ግምገማ ላይ የሚሳተፍ የባለስልጣኑ ወይም በክልል የእውቅና አሰጣጥስራን እንዲያከናውን ህጋዊ ውክልና በተሰጠው አካል የእውቅና አሰጣጥ ባለሙያ ነው፡፡ ** #ተባባሪ_(የውጭ) _ገምጋሚ ባለሙያ ማለት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትየሚያሰለጥን፡በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የሚሰራ እና በባለስልጣኑ ስልጠና ወስዶ ከእውቅና አሰጣጥ ባለሙያዎች ጋር በመሆን አንድን ማሰልጠኛ ተቋም ወይም ፕሮግራም ለመገምግም የሚሳተፍ ነው፡፡ ** #አሰልጣኝ_ማለት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ውስጥ በአሰልጣኝነት እየሰራ ያለ የዘርፉ ፕሮፌሽናል ባለሙያ ነው፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
