በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/ 2016 መሠረት ፈቃድ ወይም ፈቃድ እድሳት መሰረዝን በተመለከተ ፡-

በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/ 2016 መሠረት ፈቃድ ወይም ፈቃድ እድሳት መሰረዝን በተመለከተ ፡- ---------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------- ** ፈቃድ አግኝቶ ሲሰራ የቆየ ማንኛውም ተቋም የፈቃድ እድሳት በወቅቱ ካልጠየቀ ባለስልጣኑ ፈቃዱን ሊሰርዝ ይችላል፣ ** ማንኛውም ተቋም ወይም ፕሮግራም በባለስልጣኑ የተቀመጡ መስፈርቶችን አጓድሎ ሲገኝ እና በግምገማ ሲረጋገጥ የተሰጠው ፈቃድ ወይም ፈቃድ እድሳት ይሰረዛል፤ ** ማንኛውም በድንበር ተሻጋሪ ትምህርት መርሃ-ግብር የሚያስተምር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በዉጭ ሀገር ያለዉ ተቋም እዉቅናዉ ካልታደሰ በሀገር ዉስጥ ያለዉ ተቋም የመርሃ ግብሩ እና የትምህርት መስኩ ፈቃዱ ይሰረዛል፤ እና ** ማንኛውም ተቋም ወይም ፕሮግራም የትምህርት ጥራትን ካጓደለ፤የከፍተኛ ትምህርት አሰጣጥ ህጎችን ከጣሰ እና የእግድ ቅጣት ተላልፎበት ካላሻሻለ ባለስልጣኑ የሰጠውን ፈቃዱ ይሰረዛል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።