ለባለሥልጣኑ ሁሉም ሠራተኞች የባህሪያዊ ብቃት ምዘና እና ለድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የቴክኒካል ብቃት ምዘና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

ለባለሥልጣኑ ሁሉም ሠራተኞች የባህሪያዊ ብቃት ምዘና እና ለድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የቴክኒካል ብቃት ምዘና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------- ጥር 29 ቀን 2018 ዓ.ም በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከፌደራል ሰቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመጡ አሰልጣኞች ለባለሥልጣኑ ሁሉም ሠራተኞች የባህሪያዊ ብቃት ምዘና እና ለድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የቴክኒካል ብቃት ምዘና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ የባህሪያዊ ብቃት ምዘና ስልጠና የሰጡት በፌደራል ሰቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሰው ሀይል ብቃት መሪ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ አስፋው የመንግስት ሠራተኞች ባህሪያዊ ብቃት ጽንሰ ሀሳብ ሠራተኞች አንድን ሙያ ወይም ሥራ በመከወን ሂደት የሚኖራቸውን ማህበራዊ እና ግላዊ መስተጋብር የሰዎችን ስነልቦናዊ፣ ማህበራዊ፣ ስነምግባራዊ፣ አካላዊ ራህሮታዊና ሰብዓዊ ጉዳዮችን የሚመለከት መሆኑን ገልጸው የባህሪያዊ ብቃት አሃዶች በሆኑት አገልጋይነት፤የጊዜ አጠቃቀም፤ ተግባቦትና ተጽዕኖ መፍጠር፤ መብቃትና መነሳሳት፤ ፈጠራ፤ ሥነ-ምግባርና ተምሳሌትነት፤ የቡድን ሥራ፤ ራኅሮታዊ ብስለት፤ብዝሃነትና አካታችነት፤ እሴት ጨማሪ ሥራ፤ ኃላፊነትን መወጣት፤ ስትራቲጂያዊ አስተሳሰብ፤የገበያ ግንባታ፤የባለሚና አመራር እና መሪነት ላይ ሰፊ ማብራሪያ እና ገለጻ አድርገዋል፡፡ በፌደራል ሰቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግስት ሠራተኞች ብቃት ማረጋገጫ ኃላፊ አስፈጻሚ አቶ መሳይ ደምሴ በበኩላቸው ስለብቃት ምዘና እና ስለ ሥራ መዘርዝር ሰፊ ትንታኔና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም ለድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የቴክኒካል ብቃት ምዘናን በተመለከተ በሰጡት ማብራረያ እና ገለጻ እንደአስገነዘቡት ቴክኒካል ብቃት ማለት የመንግስት ሠራተኞችና የሥራ መሪዎች የተሰጣቸውን ተግባር ለማከናወን የሚያስፈልግ የንድፈ-ሃሳብና የተግባር እውቀትና ክህሎት መስተጋብር ሆኖ እነዚህን ተፈላጊ እውቀት እና ክህሎት ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስፈልግ ቀጥተኛና ተያያዥ ባህርይን የሚይዝ እና ሥራን በውጤታማነት ለመፈጸም የሚያበቃ ከሥራ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ያለው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የቀረቡትን መነሻ ሀሳቦች መሠረት በማድረግ በተደረገው ውይይት ላይ ለተነሱ ሐሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች በፌደራል ሰቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሰው ሀይል ብቃት መሪ ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ እና የመንግስት ሠራተኞች ብቃት ማረጋገጫ መሪ ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት በአቶ መሳይ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።