ለባለሥልጣኑ አመራሮች በዓለም አቀፍ የጥራት አመራር ስርዓት ISO9001:2015 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
-------------- ----------------------------------------------------------------------------------------
ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ለባለሥልጣኑ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በዓለም አቀፍ የጥራት አመራር ስርዓት ISO9001:2015 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በኢትዮጲያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት የስልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ አሸናፊ በቀለ በጥራት እና በደረጃ ጽንሰ ሀሳቦች፤በጥራት ምእራፎች፤ዓለም አቀፍ ስታንዳርዱ ስላካተታቸው መስፈርቶች፤ባለሥልጣኑ ISO9001:2015 ስታንዳርዶች በመተግበሩ ስለሚያገኛቸው ጥቅሞች እና ባለሥልጣኑ ከኢኒስቲትዩቱ ጋር በመተባበር በቀጣይ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ሰፊ ማብራሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የቀረበውን የስልጠና ሰነድ መሠረት በማድረግ በተደረገው ውይይት ላይ ለተነሱ ሐሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች ስልጠናውን በሰጡት በኢትዮጲያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት የስልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ አሸናፊ በቀለ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው በበኩላቸው ባስተላለፉት የማጠቃለያ መልእክት እንዳሉት ባለሥልጣኑ ዓለም አቀፍ የጥራት አመራር ስርዓት ISO9001:2015 ለመተግበር የወሰነው የጥራት ተቆጣጣሪ ተቋም በመሆኑ ፤መንግስት ለዲጅታል ዘርፉ ባለው ልዩ ትኩረት እና ቁርጠኝነት ፤በባለሥልጣኑ ከወረቀት ነጻ የሆነ አሰራርን ለመተግበር እየተሰራ በመሆኑ እና የባለስልጣኑ ሠራተኞች 5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲፍ ስልጠና ወስደው መዘጋጀታቸውን ገልጸው ዓለም አቀፍ የጥራት አመራር ስርዓት ISO9001:2015 ለመተግበር የባለሥልጣኑ አመራሮች ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
Newsroom
ለባለሥልጣኑ አመራሮች በዓለም አቀፍ የጥራት አመራር ስርዓት ISO9001:2015 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ETA
Education & Training Authority
February 06, 2026
1 min read