ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፦ አዲስ ተመዝጋቢ እና ተመራቂ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ በምትለኩበት ወቅት ሸኒ ደብዳቤያችሁ ሊኖረው የሚገባ የመረጃ ይዘት ስለማሳሰብ ይሆናል፤

ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ------ ጉዳዩ፦ አዲስ ተመዝጋቢ እና ተመራቂ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ በምትለኩበት ወቅት ሸኒ ደብዳቤያችሁ ሊኖረው የሚገባ የመረጃ ይዘት ስለማሳሰብ ይሆናል፤ ----------------------------------------------------------------------------------------------- የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ 1263/2014 ዓ.ም እና የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለማቋቋም በሚኒስትሮች ምክርቤት በወጣ ደንብ ቁጥር 515/2014 ዓ.ም መሰረት በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅ እና ለመከታተል ያስችለው ዘንድ በመመሪያ 987/2016 ዓ.ም አንቀፅ 17 ንኡስ አንቀፅ 2 መሰረት አዲስ ተመዝጋቢ እና ተመራቂ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ ወቅቱን ጠብቆ ለባለስልጣኑ መላክ እንዳለባችሁ ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም ለክትትል ይረዳን ዘንድ የአዲስ ተመዝጋቢ እና የተመራቂ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ በምትለኩበት ወቅት ሸኒ ደብዳቤያችሁ ሊይዛቸው የሚገቡ መረጃዎች ከታች ባለው ስንጥረዥ ማለትም የካምፓስ ስም ፣ የትምህርት መስኮች ስም፣ መርሃ ግብር፣ትምህርት ደረጃ እና ለያንዳንዱ ትምህርት መስኮች በመርሃ ግብርና ትምህርት ደረጃ የተማሪ ቁጥር የያዘ መሆን የሚገባ መሆን እንዳለበት እናሳስባለን፡፡