የከፍተኛ ትምህርት HEMIS የምክክር አውደጥናት ተሳታፊ መላክን በተመለከተ የተሰጠ ማሳሰቢያ
ለአድማስ ዩኒቨርስቲ ለሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ለቅ.ማርያም ዩኒቨርስቲ ለዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ለሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ ለአልፋ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለሆፕ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ለኒው ጀነሬሽን ዩኒ.ኮሌጅ ለአዲስ ኮንቲኔንታል የጤና አጠባበቅ ተቋም ለአዲስ አበባ ቢዝነስና ሜዲካል ኮሌጅ ለአዲስ ኮሌጅ ለአፍሪካ የጤና ኮሌጅ ለአትላስ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለአየር ጤና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለብራይት ኮሌጅ ለቢትስ ኮሌጅ ለሲፒዩ ቢዝነስ እና ኢን.ቴክ. ኮሌጅ ለኤግል ኮሌጅ ለኢቲ ኦንላይን ኮሌጅ ለግሬት ኮሌጅ ለሂልኮ የኮምፒዩተር ሳይ.ና ቴክ ኮሌጅ ለሀያት ሜዲካል ኮሌጅ ለጅግዳን ኮሌጅ ለክቡር ኮሌጅ ለኬቢኢንተ. የቢዝነስና ቴክ. ኮሌጅ ለሎርካን ሜዲካል ኮሌጅ ለመካነ እየሱስ ማኔጅ .ሊደር ሺኘ ኮሌጅ ለሚዩንግ ሳንግ ሜዲካል - ኮሌጅ ለሜሪላንድ ኢን. ኮሌጅ ለናሽናል አቬይሽን ኮሌጅ ለኒው አቢሲኒያ ኮሌጅ ለፕርምየም ኮሌጅ ለሰሌክት ቢዝነስና ቴክ. ኮሌጅ: ለሬነሰንስ ግሎባል ኮሌጅ ኦፍ ኦፕን እና የርቀት ት/ት ለኪዊንስ ኮሌጅ ለቅድስት ልደታ የጤና ሳይ ኮሌጅ ለሰቨን ስታር ጤና ሳይ.ቢዝ. ኮሌጅ ለዩኒቨርሳል ሜዲካል ኮሌጅ ለያኔት ኮሌጅ ለዮም የድህረ ምረቃ ኮሌጅ ለቤተል ሜዲካል ኮሌጅ ለደንበል ኮሌጅ ለሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለሳንቴ ሜዲካል ኮሌጅ ለኒው ቪዝን ኮሌጅ ለራዳ ኮሌጅ ለወርልድ ብራይት ኮሌጅ አዳማ ጄኔራል ሆስፒታል ለብሪጅ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ለአልካን የጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ለልቀት ኮሌጅ ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ ለኪያሜድ ሚዲካል ኮሌጅ ለብራይት ስታር ኮሌጅ ለሸገር ኮሌጅ ለሲልከን ቫሊ ኮሌጅ ለጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለአንድነት ቢዝነስ ኮሌጅ ለትሮፒካል ኮሌጅ ለዳይናሚክ ኮሌጅ ለዳማት ሆቴልና ቢዝነስ ኮሌጅ ለሰላም ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ለእናት ኮሌጅ ለፕሪንሲፓል የጤና እና የቢዝነስ ኮሌጅ ባሉበት ------- ጉዳዩ፡ የከፍተኛ ት/ት HEMIS የምክክር አውደጥናት ተሳታፊ መላክን ይመለከታል፤ ---------------------------------------------------------------------------- ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ዙሪያ ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ የሪፎርም ሥራዎች ዋና አላማቸው የትምህርት ጥራትን ማሻሻል ሲሆን ወቅቱን የጠበቀና ጥራት ያለው የትምህርት መረጃ በየዓመቱ በማሰባሰብ፣ በማደራጀትና በመተንተን መረጃዎችን ለፖሊሲ ቀረጻ፣ ለስትራቴጂያዊ ዕቅድ እና የእቅድ ግቦች ተአማኒነት ባለው መረጃ ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ መስራት አንዱ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሪፎርም ሥራዎች ያሉበትን ሁኔታ እና በቀጣይ ምን መሰራት እንዳለበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን መስራት ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም የ2018 ዓ.ም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከሪፎርም ሥራ አንፃር እና መረጃ አሰባሰብ ያለበት ሁኔታ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሪፎርም ስራዎችን የተመለከተ የምክክር እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል። ይህንን ስራ ለመተግበር ከታህሳስ 14-15/2018 ዓ.ም. የመረጃ ማጥራትና መረካከብ አውደ ጥናት ተዘጋጅቷል።ስለዚህ የተቋማችሁን የተሟላ መረጃ በመያዝ ከስራው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው አንድ ባለሙያ እና የተቋሙ ባለቤት ወይም የበላይ አመራር ለስራ የሚሆን ላፕቶፕ ኮምፒውተር በመያዝ እና ወጪያቸውን በመሸፈን በታህሳስ 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 በትምህርት ሚኒስቴር ትንሹ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲገኙ አሳስባለሁ።
