#ማሳሰቢያ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፦ በ2018 ዓ/ም የተመዘገቡ አዲስ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ እንድትልኩ ስለማሳሰብ ይሆናል፤
#ማሳሰቢያ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ------- ጉዳዩ፦ በ2018 ዓ/ም የተመዘገቡ አዲስ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ እንድትልኩ ስለማሳሰብ ይሆናል፤ -------------------------------------------------------------------------------------------- የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ 1263/2014 ዓ.ም እና የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለማቋቋም በሚኒስትሮች ምክርቤት በወጣ ደንብ ቁጥር 515/2014 ዓ.ም መሰረት በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅ እና ለመከታተል ያስችለው ዘንድ በመመሪያ 987/2016 ዓ.ም አንቀፅ 17 ንኡስ አንቀፅ 2 መሰረት አዲስ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ ወቅቱን ጠብቆ ለባለስልጣኑ መላክ እንዳለባችሁ ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም በተቋማችሁ ፈቃድ በተሰጣችሁ ትምህርት መስኮች፣ ትምህርት ደረጃ፣ መርሃ ግብር እና ካምፓስ በ2018 ዓ.ም የመዘገባቸውን አዲስ ተማሪዎች ብቻ ከዚህ በፊት በተላከው ቅጽ መሰረት ዝርዝር መረጃውን እስከ ታህሳስ 25/ 2018 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡
