በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት በባለሥልጣኑ ከተሰጠው የደረጃ ስያሜ ውጪ ሌላ የደረጃ ስያሜ ሲጠቀም የተገኘ ተቋምን በተመለከተ:-
በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት በባለሥልጣኑ ከተሰጠው የደረጃ ስያሜ ውጪ ሌላ የደረጃ ስያሜ ሲጠቀም የተገኘ ተቋምን በተመለከተ:- ======== ======== ======== ======= ===== ======== ======= = ======== ======= ========== ======== ======== ** ማንኛውም ተቋሙ ከባለሥልጣኑ የተሰጠውን የደረጃ ስያሜ ለውጦ መገልገል አይችልም፤ ** በባለሥልጣኑ ያልተሰጠውን የደረጃ ስያሜን በመጠቀም የሰጣቸውን የትምህርት ማስረጃዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያስተካክል ይደረጋል፣ ** ህጋዊ ያልሆነ ስያሜውን በበራሪ ወረቀቶች፣ በማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በሌላ በማናቸውም መረጃ ማስተላለፊያ ዘዴዎች ለህዝብ ይፋ አድርጎ ከሆነ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማስተካከያውን በተመሳሳይ ዘዴ ወይም ሚዲያ እንዲገለፅ ያደርጋል፤ ይህንን በተግባር ለመፈፀም በመረጃ የተደገፈ ሪፖርት ለባለስልጣኑ ያቀርባል፣ ** ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራዊ ያለማድረጉ ሲረጋገጥ ተቋሙ ለ2 ዓመታት የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት እንዳይሰጥ ቅጣት ይጣልበታል፡፡ ተማሪዎችን ፈቃድ ወዳላቸው ተቋማት በ1 ወር ጊዜ ውስጥ አዛውሮ ሪፖርት ያደርጋል፤ ** ከላይ የተጠቀሰውን የተላለፈ ተቋም እንዲዘጋ ይደረጋል፤ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
