ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፡- በ 2018 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው የመዉጫ ፈተና የሚፈተኑ ብቁ እጩ ተፈታኞች መረጃ ስለመጠየቅ፤
ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ------ ጉዳዩ፡- በ 2018 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው የመዉጫ ፈተና የሚፈተኑ ብቁ እጩ ተፈታኞች መረጃ ስለመጠየቅ፤ --------------------------------------------------------------------------------------------- የትምህርት ሚኒስቴር ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የመውጫ ፈተና በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የመውጫ ፈተና በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ ፈተናውን በዓመት ሁለት ጊዜ መሰጠት እንዳለበት የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 919/2014 ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለትምህርት ሚኒስቴር በቀን 2/04/2018 ዓ/ም በቁጥር01//ተ_21/01/1090/18 በተፃፈ ደብዳቤ የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና በዓመቱ አጋማሽ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡በዚሁ መሰረት የተፈታኞች ምዝገባ ከ6-13/04/2018ዓ/ም ለማካየድ የታቀደ በመሆኑ አስፈታኝ ለሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምዝገባ ከ 6_13/04/2018ዓ/ም ስለሚካሄድ በተጠቀሰ ቀን ላይ ብቻ የተፈታኞች እንዲመዘገቡ አስፈላጊውን እንዲያደርጉልን በማለት አሳውቋል፡፡ ስለሆነም በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ እጩ ተፈታኞች ለማጣራት እንዲቻል ዘንድ በተቋማችሁ ፈቃድ በተሰጣችሁ ትምህርት መስኮች፣ ትምህርት ደረጃ፣ መርሃ ግብር እና ካምፓስ በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ እጩ ምሩቃን ዝርዝር መረጃ ከዚህ ደብዳቤ አባሪ በተደረገ ቅፅ መሰረት ዝርዝር መረጃውን ከ6_13/04/2018ዓ/ም ከዚህ በፊት በምታስገቡበት ሲስተም እንደታስገቡ እናሳስባለን፡፡ ቅጹን ለማግኘት ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇https://t.me/FDRE_ETA/2505 ወይም https://docs.google.com/.../1Tr8y5NFttBIwSQEwOfeG.../edit...
