ለባለሥልጣኑ መካከለኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በአገልግሎት ስነ-ምድብ/ሰርቪስ ታክሶኖሚ/አዘገጃጀት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለመሪ ሥራ አስፈፃሚዎች፣ ለዴስክ ኃላፊዎች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች በአገልግሎት ስነ-ምድብ/ሰርቪስ ታክሶኖሚ/ አዘገጃጀት ላይ የተሰጠውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በንግግር የከፈቱት በባለሥልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽንና የብቃት ማረጋገጫ መሪ ሥራ አስፈጻሚ እና የባለሥልጣኑ የሪፎርም ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ሀብታሙ ተሾመ የሪፎርሙ ዓላማ አገልግሎት አሰጣጣችን ለማሻሻል እና ለማዘመን መሆኑን ገልጸው ሀገራችን የጀመረችውን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ በባለሥልጣኑ የተቋማዊ ለውጥ ሥራ አስፈጻሚ እና የባለሥልጣኑ የሪፎርም ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ደስታ ተክለአረጋይ በበኩላቸው በአገልግሎት ስነ-ምድብ/ሰርቪስ ታክሶኖሚ/ አዘገጃጀት ላይ የተዘጋጀውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሠረታዊ ዓላማ የአገልግሎት ምንነት፣ የተገልጋይ ዓይነቶች ፤የአገልግሎት ስነ-ምድብ ዓላማ፣ አስፈላጊነትን እና ተዋረዳዊ መዋቅሩን እና የሴክተሩን የአገልግሎት ስነ-ምድብ በቴንፕሌቱ መሠረት ማዘጋጀት ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአገልግሎት ስታንዳርድ፣ ፍሰት፣ ማፒንግ እና ካታሎግን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡት በባለሥልጣኑ የከፍተኛ ትምህርት የጥራት ኦዲት ዴስክ ኃላፊ እና የባለሥልጣኑ የሪፎርም ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ዐብይ ገዛኸኝ የስልጠና መሠረታዊ ዓላማ የአገልግሎት ስታንዳርድ አዘገጃጀት፤ የአገልግሎት ፍሰትና ማፒንግ እና ካታሎግ አሰራር ዝግጅት ላይ ግንዘቤ ማስጨበጥ እና ተገቢ እውቀት እንዲኖር ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የስልጠናው ተሳታፊዎች በየሥራ ክፍላቸው እየሰጡ ለሚገኙት አገልግሎቶች ስታንዳርድ የማዘጋጀት ተግባራዊ ሙከራ እንዲያደርጉ ተደረጎ ገብአት የማሰባሰብና ግልጽ መሆን በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ እና ምላሽ በሪፎርም ኮሚቴው ሰብሳቢ እና በአሰልጣኞች ተሰጥቷል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
