ማሳሰቢያ ለሁሉም የቴ/ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት/ኮሌጆች ባሉበት ጉዳዩ- የሰልጣኞች ዝርዝር መረጃ እንድትልኩ ስለማሳሰብ፡

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፐብሊክ የፌደራል መንግስት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 አንቀፅ 60(1) እና የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለማቋቋም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 515/2014 በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር መነሻ በማድረግ በፌዴራል፣ በውጭ አገርና በወጭ ባለሀብት ደረጃ ለተቋቋሙ የቴ/ሙያ ት/ስ ተቋማት ፈቃድ የሰጠ ሲሆን ፈቃድ የወሰዱትን የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ጥራት በላቀ ደረጃ ለማስጠበቅ እና ለመከታተል ያስችለው ዘንድ የከፍተኛ እና የቴ/ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር-987/2016 አጸድቆ በስራ ላይ እንዲውል አድርጓል፡፡ በመሆኑም በመመሪያ ቁጥር-987/2016 በክፍል ሶስት በቴ/ሙያ ዘርፍ አንቀፅ 29 ንዑስ አንቀፅ 1እና2 መሰረት የትምህርትና ስልጠና ተቋማት በስልጠና ዓመቱ የመዘገቡዋቸውን የአዲስ ሰልጣኞችን እና አጠናቃቂ/ተመራቂ ሰልጣኞች መረጃ በተሟላና በአግባቡ መያዝ፤ መጠበቅ እና ለሚመለከተው አካል በተቀመጠውና በተጠየቀበት ወቅት በሚዘጋጀው ቅጽ ወቅቱን ጠበቆ መላክ እንዳለባችሁ የተደነገገ በመሆኑ ከዚህ ደብዳቤ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ መሰረት የሰልጣኞችን ዝርዝር መረጃ ለይታችሁና አደራጅታችሁ በታተመ እና ባልታተመ ቅጅ /hard & Soft Copy/ እስከ ህዳር 15/2018 ዓ.ም ድረስ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡