የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ አገልግሎት ለማግኘት የሚያመለክቱ ተገልጋዮች የሚከተሉትን ቅድመ-ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል!
1. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል/temporary / ዲግሪ፤ 2. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ትራንስክሪፕት/Student Copy/፤ 3. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘ ኦሪጅናል ዲፕሎማ ወይም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት፤ 4. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ከሆነ በሀገር አቀፍ የት/ት ምዘናና ፈተናዎች አገልገሎት ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ ፤ 5. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው ዲፕሎማ ከሆነ ዲፕሎማው በተገኘበት ክልል የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ወይም የዞን/የከተማ መስተዳደር የሥራና ስልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (COC) ፤ 6. የዲግሪ መግቢያው ከውጭ በተገኘ የትምህርት ማስረጃ ከሆነ ከባለስልጣኑ የተገኘ የአቻ ግመታ ደብዳቤ፤ 7. የሁለተኛ/የማስተርስ/ ዲግሪን ለማረጋገጥ ከሆነ ደግሞ በቅድሚያ የመጀመሪያው ዲግሪ ከላይ በተገለፀው መንገድ መረጋገጥ ይኖርበታል፤ 8. የስም ለውጥ ካለ የፍርድ ቤት ውሳኔ የተላፈበት ማስረጃ፤ 9. የማመልከቻ ክፍያ በኤሌክትሮኒክ ክፍያ በቴሌ ብር እና በሲኢቢ ብር ፤ 10. ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የፋይዳ ልዩ ቁጥር FIN፤ 11. ስካን (Scan) የተደረገ ሶስት በአራት (3x4) ጉርድ ፎቶግራፍ እና 12. ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉም ማስረጃዎች አንድ አንድ ስካን (Scan) በማድረግ ባሉበት ሆነው በበይነ መረብ https://neta.gov.et ማስፈንጠሪያን በመጠቀም ማመልከት ይችላሉ፤ በተጨማሪም ቀጠሮ አስይዘው በአካል ሲመጡ በባለጉዳዩ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሰነድ ባላቸው ተወካዮች አማካኝት ሁሉንም የትምህርት ማስረጃ ዋናውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ