ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተውጣጡ ለነርሲንግ ፕሮግራም የትምህርት ክፍል ተጠሪዎችና ባለሙያዎች በእውቅና አሰጣጥ ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ

የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የእውቅናና አሰጣጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ ከጤና ሚንስቴርና ከትምህርት ምኒስቴር ጋር በመተባበር በሁለት ዙሮች ለ80 ሰልጣኖች በእውቅና አሰጣጥ ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና በአዳማ ከተማ ለ6 ቀናት ተሰጠ ፡፡ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ጽንሰ ሀሳብ ፣ የእውቅና አሰጣጥ ስታንደርድ ፣የእውቅና አሰጣጥ ሂደቶች ፣የእውቅና አሰጣጥ መሳሪያዎች እና ተያያዥ ነጥቦች ላይ ትኩረት ባደረገው የሥልጠና መረሀ ግብር ላይ በባለሥልጣኑ የእውቅናና ስታንደርዳይዜሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ፤ የእውቅና አሰጣጥ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተረፈ በላይ እና የእውቅና ዴስክ ኃላፊዎች እና ባለሙያ እንዲሁም ከጤና ሚኒስቴርና ከትምህርት ምኒስቴር የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆነ ዋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በተሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ