ማስታወቂያ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፡- የዳግም ምዝገባ ዝግጅት ይመለከታል

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚያግዙ የተለያዩ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ዘዴዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያና ማሻሻያ ዘዴዎች መካከል አንዱ የፈቃድ አሰጣጥ ነው፡፡ ይህንን የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ዘዴ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ መመሪያ እና ስታንዳርድ ጸድቆ ስራ ላይ ውሏል። በመሆኑም መመሪያና ስታንዳርድ ተግባራዊ ለማድረግ በከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/2016 አንቀጽ 4(26) መሠረት ሁሉንም በስራ ላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በፌደራል ደረጃ ፈቃድ የተሰጣቸው ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ለዳግም ምዝገባ መዘጋጀታችንን ሀምሌ 22/2016 ዓ.ም ባደረግነው ስብሰባ መግለጻችን ይታወሳል። በዚህ መሠረት ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዳግም ምዝገባ መምሪያ መሰረት እስከ ነሃሴ 30/2016 ዓ.ም በተቋም፣ በካምፓስ እና በፕሮግራም ደረጃ በሀርድ ኮፒ እና ሶፍት ኮፒ የተደራጁትን መረጃዎች በአካል በመቅረብ እንዲሁም በየጊዜው በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት መረጃዎችን እንድታደራጁ እና በቂ ዝግጅት በማድረግ እንድታመለክቱ አጥብቀን እናሳስባለን። በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ