የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የሀገራችን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የአየር ንብረትን በማመቻቸት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ
ሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም የትምህርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ የሁኑት የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እና የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት በጋራ በመሆን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምሥራቅ ሸዋ ዞን ሎሜ ወረዳ ባደረጉት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የአረንጓዴ አሻራ መረሀ የሀገራችን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የአየር ንብረትን በማመቻቸት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ገልጸዋል ፡፡በመረሀ ግብሩ ላይ ለስሬ ሊበን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተደረገው የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸው የአካባቢው ማኅበረሰብ ለተተከሉት ችግኞች እንክብካቢ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራን ማኖር የአየር ንብረት ተጽእኖን ለመቋቋም የሚያስል መሆኑን ገልጸው አረንጓዴ አሻራን ማኖር አገር የሚያሻግር ኢትዮጵያን ወደፊት የሚወስድና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ተግባር ነው ብለዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራ ማኖር ድርቅንና ተጓዳኝ ችግሮችን ለመቋቋም የሚያስች ተግባር መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ግርማ ባይሳ የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ላደረጉት የችግኝ ተከላ እና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አመስግነው የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ