ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፡- የስብስባ ጥሪን ይመለከታል

ተቋማችን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በደንብ ቁጥር 515/2014 በተሰጠው ሥልጣን እና ተግባር መሠረት የከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ካዘጋጀ በኋላ አጽድቆ በሥራ ላይ እንዲውል አድረጓል፡፡ ይህንን መመሪያ ተከትሎ ዝርዝር አሠራር የሚገልጽ ስታንዳርድ አዘጋጅቶ በባለሥልጣኑ ቦርድ እንዲጸድቅ አድርጓል፡፡ መመሪያውንና ስታንዳርዱን ማዘጋጀት ያስፈለገበት ዋና ምክንያት የትምህርትና ስልጠና ጥራትን ለማሻሻል እንዲሁም ለተገልጋዮች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያሥችል ግልጽ አሠራር ለመዘርጋት ታስቦ ነው፡፡ ይህንን መመሪያና ስታንዳርድ ተግባራዊ ለማድረግ በከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/2016 አንቀጽ 4 (26)መሠረት ሁሉንም በሥራ ላይ ያሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ ማካሄድ በማስፈለጉ ይህንኑ ለማስፈጸም የተዘጋጁ የዳግም ምዝገባ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡ በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት አሠራሮች ላይ ግልፀኝነት ለመፍጠርና የዳግም ምዝገባ ሂደት ለማስረዳት ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ በተዘጋጀው ስብሰባ ሁሉም ተቋማት ባለቤት ወይም አንድ ተወካይ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት እንዲገኙ እናሳስባል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ