ማሳሰቢያ ለሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት

ጉዳይ፡- የመመሪያና ስታንዳርዶች ረቂቅ ሰነድ ውይይት ላይ እንድትገኙ ስለመጋበዝ፤ ባለስልጣኑ የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የጥራት ኦዲት መመሪያ እንዲሁም የጥራት ኦዲት እና የእውቅና አሰጣጥ ስታንዳርዶች ረቂቅ ሰነድ አዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም በረቂቅ ሰነዶቹ ዙሪያ ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 አዲስ አበባ በሚገኘው ስካይ ላይት ሆቴል በሚካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የሚሳተፍ የተቋሙ የበላይ ኃላፊ ወይም ተወካይ የሆነ አንድ ተሳታፊ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት እንድትልኩ እያሳወቅን የትራንስፖርት እና የውሎ አበል የማንሸፍን መሆኑን እናሳስባለን፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ